
Saro የተሰኘውን የማህበራዊ ትስስር መተግበርያ በማበልፀጋችን ኩራት ይሰማናል!
"ፍቅር በሕይወት " የሕፃናትና ወጣቶች የልማት ድርጅት የወጣቶች የሠላም፣የልማት ግንባታና የተሞላ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሦስት አመት ፕሮጀክት ማጠቃለያ ወርክሾፕ አዘጋጀ
ድርጅቱ ከBena Soft System ጋር ያበለፀገውና የጋሞ ሕዝብ የሠላም እሴቶች ፣በጎነትና መተባበርን የሚያንፀባርቁ ይዘቶች የሚተላለፉበት ' Sarro App' የዲጂታል መተግበሪያ በይፋ አስጀምሯል
Play Store Download Link: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.benasoft.saro
አርባምንጭ ፣ መስከረም 8/2019 ዓ፣ም(አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)፦
የድርጅቱ የካንተሪ ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ጋጋሎ በወርክሾፑ ባስተላለፉት መልዕክት "ፍቅር በሕይወት ኢትዮጵያ " የሕፃናትና ወጣቶች ልማት ድርጅት ላለፉት 20 አመታት በአርባምንጭ ከተማ በልማት፣በመልካም አስተዳደር፣በሠላም ግንባታና በተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ ሥራዎች እየሰራ የቆየ ድርጅት መሆኑ ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ባሉት ማዕከላት ከዓለምአቀፍ የተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር በተለያዩ ፕሮግራሞች እየሰራ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ የልማት ድርጅት መሆኑን ጠቁመዋል።
ባለፉት ጊዜያት የሠላም እሴትን ከጋሞ ሕዝብ ተምሳሌትነት መነሻ በማድረግ ለወጣቶች በልማትና በሠላም እሴት ግንባታ እንዲሁም ኃላፊነት የተሞላ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችንና ለሴቶችና ሕፃናት ማህበራዊ ድጋፎችንና የሥራ ዕድል ፈጠራን እያከናወነ መቆየቱን አስረድተዋል።
ድርጅቱ ከGIZ CPS IDP ፕሮግራም ጋር በመተባበር በከተማዋ በነበረው የሦስት አመታት የሥራ ላይ ቆይታ በወጣቶች የሰላም ግንባታ ሚናቸውን ለማጎልበት በርካታ ተግባራት ሲከወኑ መቆየቱን አውስተው የፕሮጀክቱ መገባደጃ ወቅት ላይ እንደመሆኑ የተሰሩ ሥራዎችን በመገምገም የተጀመረውን የወጣቶች የሠላም እሴት ግንባታን ሂደት ቀጣይነት እንዲኖረው ለተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት፣ለወጣቶችና ለወጣት አደረጃጀቶች እንደባለድርሻ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህንን የሠላም ግንባታ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሠላም ተምሳሌትና የሠላም እሴቶች የተሞላው የጋሞ ሕዝብን ተሞክሮ እንዲወሰድበት በማሰብ ድርጅቱ ከBena Soft System ጋር ያበለፀገው Sarro App' የዲጂታል መተግበሪያ ማስጀመሪያ መርሃግብር ያለው በመሆኑ ለድርጅቱም ሆነ ለአርባምንጭ ከተማ ታሪካዊ ዕድል መሆኑንም አመላክተዋል።
መተግበሪያው ማንኛውም የስማርት ስልክ ተጠቃሚ ለሆነ ለሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል መጠቀም በሚችሉት መልኩ የበለፀገ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ ወጣቱን አሉታዊ ተፅዕኖ ከሚፈጥሩበት ማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ለመጠበቅ የጋሞ ሕዝብ የሠላም እሴቶች ፣በጎነትና መተባበርን የሚያንፀባርቁ
የሠላም ግንባታ ይዘቶችን ወጣቱ የሚለዋወጡበት መተግበሪያ እንደሆነም ገልፀዋል።
ድርጅቱ የሥራ ዕድል ፈጠራን ጨምሮ በሌሎች ፕሮግራሞች ሰፊ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉት ዳይሬክተሩ በከተማው በነበረው በቆይታም የወጣቶች የሰላም ካውንስል እንዲቋቋም በማስቻሉ የወጣቶች አደረጃጀትና ሌሎች የዘርፉ ባልድርሻዎችጋር የተጀመረውን የሠላም ግንባታ በተጠናከረ መንገድ እንዲቀጥል በቅርበት ይደጋፋልም ብለዋል።
አቶ የሱነህ ሳሙኤል የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው ፍቅር በሕይወት " የሕፃናትና ወጣቶች የልማት ድርጅት ለከተማዋ ወጣቶች የተሞላ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ የልማትና የሰላም ምስረታ ስልጠና ሲሰጥ፣ የስራ ዕድል ፈጠራን ሲደግፍ መቆየቱን ገልፀዋል።
በወጣቱ ዘንድ የሠላም ግንባታ እንዲሰርፅ፣የልማትና የበጎነት እሳቤዎች እንዲጎለብቱ ያለሰለሰ ጥረት ያደረገ ድርጅት መሆኑን ጠቅሰው ይህንን የተጀመረውን የሰላም ግንባታ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የወጣቶች ኃላፊነት ከፍተኛ ቢሆንም የባለድርሻ አካላት እገዛና ድጋፍም እንዲጠናከር ያደረገዋል ብለዋል።
ድርጅቱ በከተማዋ በነበረው ሥራ ቆይታ በሠላም ግንባታ ሂደት በወጣቱ ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን በማምጣቱ ሊመሰገን ይገባልም ብለዋል።
በድርጅቱ የሦስት አመታት አበይት ተግባራት በመድረኩ የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎችም የማጠናከሪያ ሀሳቦችን የሰጡ ሲሆን የተጀመረው የወጣቶች የሠላም ግንባታ ሂደት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልፀዋል።
ወጣቱ ኃላፊነት ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ በመሆን ማህበረሰቡን ይበልጥ የሚጠቅም እንዲሆን በሰላም ግንባታ እንደሌሎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች አርአያ በመሆን ሌሎችን ማስተማርና ማፍራት ይጠበቃልም ብለዋል።
በአዲሱ 'የሳሮ አፕ' የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም የአካባቢያቸውን ገፅታ ለመገንባትና ትክክለኛ የመረጃ መለዋወጫ ፕላትፎርም አድርገን እንጠቀማለን በማለት አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል።
የማጠቃለያ ወርክሾፑ በጋሞ አባቶች ምረቃትና ምክር የተጀመረ ሲሆን ፍቅር በሕይወት " የሕፃናትና ወጣቶች የልማት ድርጅት ኦፊሰሮችና አስተባባሪዎች፣የBena Soft System ከፍተኛ ባለሞያዎች፣የከተማው ባለድርሻ ተቋማት፣የማህበራዊ ሚዲያ የይዘት ፈጠራ ወጣት ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።
via በጌታ ፈቀደ